Monday, 9 May 2016

A-square DSTV

A-Square  DSTV
     ይህ ኤ ስኩዌር ተብሎ የተፃፈ ከፊደል ግድፈት የተያያዘ ስለሆነ ትክክለኛ መልእክት ምን እንደሆነ ግልፅ አይደለም ምን ለማለት እንደፈለገ ለመረዳት ይከብዳል ለራሡ እንኳን ቢገባው ለሌላ ሠው ትርጉም አልባ ነው የሚሆነው ምክንያቱም በመሀሉ የቀረ ፊደል ወይም ሀሣብ ስላለው ለሌላ ሠዎች በቀላሉ ለመረዳት ይከብዳል ፡፡
      ስለዚህ እነዚህ በፊደል ግድፈት የሚፃፉት ቢል ቦርዶች ትክክለኛ መልእክት እዛቤት እንዳይስተላለፍ ትክክለኛ መልእክት ካልተላለፈ ደግሞ ተጠቃሚዎች ለዚህ ድርጅት በቀላሉ ሊቀንሡ ይችላሉ ምክንያቱም እንነዚህ በፊደል ግድፈት የተፃፉ ቢል ቦርዶች አብዛሀኛው ሰዎች ለማወቅ ይቸገራሉ ፡፡
       ሌላው ችግር ደግሞ ኤ- ስኩዌር ዲኤስ ቲቪ የሚለው ቢል ቦርድ በእንግሊዘኛ ኤ ስኩዌር ዲኤስ ቲቪ ተብሎ ተፅፎ ይገኛል እዛላይ የሚገኙ ሞስሎች ደግሞ ለኛ ሆነ ላገራችን ምስልና ማንነት የማይገልፁ ናቸው ይሁን እንጂ አንዳንድ ሰዎች ምሰላቸውና ፎቷቸው ሲያዩት ሲያደንቋቸው እናያለን የዚህ ምክንያት ደግሞ የማንነታችን አለማወቅ ችግር ነው ብዬ አምናለሁ፡፡
          ስለዚህ እንደዚህ ያሉት በግድፈት ፊደል የተፃፉ እና በእንግሊዘኛ ቋንቋ የተጻፋት ቢል ቦርዶች የተሣሣተ አመለካከት ያላቸው ነገሮች በራሣችን ቋንቋና ማንነት ተቀይረው ቢጻፉ ለኛ ሆነ ላገራችን እድገት ጠቃሚ ነው ብዬ አምናለሁ፡፡

No comments:

Post a Comment