Online Cafe
ይህ ካፌ ኦንላየን ካፌ ተብሎ በእንግሊዘኛ ቋንቋ ተለጥፎ ይታያል ለምን በእንግሊዘኛ ተፃፈ? ለምን ባማረኛ አይፃፍም? ይህ ባለቤት እንደ ተሣሣተ ያቃል እንዴ ብዬ ለራሴ ጥያቄ ስጠይቅ እዚህ ቤት እንደተሣሣተ አምናለሁ ፡፡
ስለዚህ ይህ ቤት ኦን ላይን ካፌ ተብሎ የተለጠፈበት የተለያዬ ተጠቃሚዎች እዚህ ካፌ ችግር ሊያስከትል ይችላል ምክንያቱም ይህ የካፌው ስም በእንግሊዘኛ ቋነቋ ስለተፃፈ እንዲሁም እንግሊዘኛ ማንበብ የማይችሉ ሰዎች ወደዚህ ቤት ለመግባት ሊያስቸግራቸው ይችላል፡፡
ስለዚህ ድርጂቱ በሌላቋንቋ ከመሠየም ይልቅ ጉዳቱ ስለሚያመዝን በተለይም እነዚህ በእንግሊዘኛ የተጻፉ ማስታወቂያዎች ተጠቃሚ ማህበረሰብ ለመረዳት ስለሚያስቸግሩ ለህብረተሠቡ ያደናግራሉ ፡፡
ስለዚህ እንደኔ አስተሳሰብ ድርጅታችን በራሳችን ቋንቋ ተጠቅመን ስያሜ ብንሰጠው ይበልጣል የሚል አስተሣሠብ አለኝ ምክንያቱም ለእድገት አንድ ሀገር አስፈላጊ ከሚባሉት ነገሮች አንድ ቋንቋ ስለሆነ ህብረተሠቡ በቀላሉ ሊጠቀም ይችላል ስለዚህ አንድ ማስታወቂያ ግቡን ሊመታ የሚችለው ተጠቃሚው እና አገልግሎት ሰጪ ሊግባባ በሚችለው ቋንቋና ቦታ በተገናኘበት ነው ብዬ አምናለሁ፡፡
Monday, 9 May 2016
Online cafe
Subscribe to:
Post Comments (Atom)
No comments:
Post a Comment